Karalo Secondary School
Announcement አስደሳች ዜና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ

አስደሳች ዜና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ

11th December, 2025

ቀን 02/04/2018

አስደሳች ዜና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ በዛሬው እለት በተካሄደው የወንዲራድ ክላስተር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድር በከፍተኛ ፉክክር እና መለያ ጥያቄዎች የካራአሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአንደኛ ደረጃ በመያዝ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ተማሪዎች አንደኛ እና ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ የምስክር ወረቀት እና ገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ። ሁለቱ ተማሪዎች ክላስተር በመወከል ለክፍለ ከተማ የሚወዳደሩ ይሆናል ። ለዚህ ውጤት መመዝገብ የተማሪዎች ፣ የመምህራን ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች ፣ ወተመህ አካላት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ። ይህም ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑ ማሳያ ሲሆን የትምህርት ቤቱን ገፅታ ከመገንባት አንፃር ጉልህ ድርሻ አለው ። መምህራን ውጤት ማሻሻል ላይ በተሰራው መጠን በመናበብ ለአንድ ዓላማ በመቆም በስነምግባር ላይም ትኩረት ሰጥቶ በመስራት እመርታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው ። በዚህ መጠን ከተሰራ ትምህርት ቤቱ በአጭር ጊዜ ተመራጭ ማድረግ ይቻላል ። ስለዚህ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይህንን መነሻ በማድረግና ዒላማ በማስቀመጥ መስራት ይኖርብናል ። ጠንክሮ መስራት ውጤታማ ያደርጋል ።

እንኳን ደስ አላችሁ


.

Copyright © All rights reserved.

Created with