Karalo Secondary School
Announcement የሪሜዲያል ፕሮግራም የተቋም ምደባ ይፋ ሆናል።

የሪሜዲያል ፕሮግራም የተቋም ምደባ ይፋ ሆናል።

30th October, 2025

(ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም) ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ማድረጉን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡


በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደዉ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸዉን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡


ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንዲከታተሉም አስታዉቋል፡፡

ተማሪዎች የተመደቡበተን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች
1. Website:
 https://student.ethernet.edu.et
2. Telegram bot: @moestudentbot መሆናቸዉን ትምህርት ሚኒስቴር ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with