Karalo Secondary School
Announcement አዋጭ ፋውንዴሽን ለካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሴት ተማሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ አደርገ ፡፡

አዋጭ ፋውንዴሽን ለካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሴት ተማሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ አደርገ ፡፡

23rd June, 2025

አዋጭ ፋውንዴሽን ለካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሴት ተማሪዎች  ለሁለተኛ ጊዜ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ አደርገ ፡፡
አዋጭ ፋውንዴሽን ከአዲስ አበባ ት/ቢሮ ጋር በጋራ የሚሠራ በመሆኑ የአ.አ ት/ቢሮ ባደረገው ጥቆማ ለካራአሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አድራሻ የካ ክ/ከ/ወ/12 በመሄድ ከአዲስ አበባ ት/ቢሮ ከፕሮጀክት ክፍል ከመጡ ባለሙያ እና  ከት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አንዳርጋቸው  ግርማ  እና ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ በረከት አብ ደበበ  ጋር ውይይት ተደርጎ ትምህርት ቤቱ በሚለየው /በሚያደርገው ምልከታ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰብ   ልጆች   የሚሰጥ አንድ መቶ ካርቶን፣በቁጥር ሁለት ሺህ አራት መቶ የሚሆን  የንህፅና መጠበቂያ ሞዴስ አዋጭ ፋውንዴሽን  ድጋፍ አደርጓል ፡፡ በዕለቱ የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ጠጅነሽ የተገኙ ሲሆን አዋጭ ፋውንዴሽን በተለያዩ ወረዳዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው ፋውንዴሽኑንና አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ሕ/ሥ/ማህበርን አመስግነዋል ፡፡ በስነ-ስርዓቱ ተሳታፊ የነበሩ መምህራን ስለገንዘብ ቁጠባ ሕብረት ሥራ ማህበር አባል ስለሚሆንበት እና የብድር ተጠቃሚ ስለሚሆኑበት ጥያቄ አቅርበው ገለፃ ተደርጎላቸዋል ፡፡


.

Copyright © All rights reserved.

Created with