ቀን 07/03/2018 ዓ.ም
የትምህርት ስራ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ያካተተ ሆኖ ተማሪዎች በአካል የዳበሩ፣ ማህበራዊ መስተጋብራቸው የሚተሳሰርበት፣ በአእምሮ የሚጎለምሱበት፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት የሚጎለብትበት፣ እርስ በመከባበር በጋራ ተግባራትን የሚያከናዉኑበት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት ጤንነታቸውን የሚጠብቁበት፣ በተጨማሪም የአካባቢው ማህበረሰብ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግና በተቋሙ እንደራስ የሚጠቀምበት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የት/ቤቱ ወተመህ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከት/ቤቱ አመራርና ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ መ/ራን ጋር በመተባበር ተማሪዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በንድፈ ሃሳብ ከተማሩት ባሻገር በአግባቡ በተግባር መከወን የሚያስፈልጋቸው መሆኑን በመረዳት በዛሬው እለት ግሬደርና ዶዘር በማስገባት የስፖርት ሜዳው ምቹ እንዲሆን ሙሉ ወጪውን በመሸፈን የማስተካከል ስራ ሰርተዋል፡፡ ይህም በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ የት/ቤቱ መ/ራንና ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና የአካባቢው ወጣቶች ከአልባሌ ቦታ በመራቅ ስፖርታዊ ጨወታዎችን ማከናወን እንደሚችሉ እንገልፃለን፡፡
ስራውን በሙሉ ኃላፊነት ለተወጡ ወተመህ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እያመሰገንን በቀጣይም በተማሪ ስነ ምግባርና ዉጤት መሻሻል ተግባራት ላይ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነታችን ነው፡፡
ት/ቤቱ



.