Karalo Secondary School
Announcement በኢፊደሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

በኢፊደሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

28th March, 2025


በአካዳሚክ ምክንያት ከአንድ ተቋም የተባረረ ተማሪ ወደ ሌላ ተቋም ሲመዘገብ ቀድሞ በተባረረበት ተቋም ያገኘው ውጤት እንደማይያዝለት ተናገሩ
      የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካዳሚክ ምክንያት ለተባረረ (dismissed) ተማሪ የኮርስ ኤግዘምሽን በተመለከተ አዲስ መመሪያ በላከው ደብዳቤ አስታውቃል።
         ባለስልጣኑ በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ስልጣን ተሰጥቶታል።
            በተሰጠው ስልጣንም በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት ማንኛውም ተቋም ስልጣን ባለው አካል የወጣ የቅበላ መስፈርት ያለሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደማይቻል ደንግጓል፡፡ አንድ ተማሪ በአካዳሚክ ምክንያት ከአንድ ተቋም በሚባረርበት ጊዜ ተማሪው ብቁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው።

            በዚህም ተማሪው በአዲስ መልክ ሌላ ተቋም ውስጥ በትምህርት ዘመኑ በተቀመጠው የመቁረጫ ነጥብ ውጤት የሚያስገባው ከሆነ ተመዝግቦ ቢማር ቀድሞ በተባረረበት ተቋም በአንዳንድ ኮርስ ያገኘው ውጤት ኤግዘምት የማይደረግ በመሆኑ ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማሳስቢያ ተሰጥቷል።


.

Copyright © All rights reserved.

Created with