የካራሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዛሬ ሰኔ 14 2018 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በ6 የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች የየካ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አንነህ ዮሴፍ በተገኙበት በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ከትምህርት ሚንስተር በወረደ መመሪያ መሰረት በደረጃ 1 በደመቀ ሁኔታ አሰመርቋል።
የዕለቱ መርሃ ግብር ያማረ እንዲሆን ያስተባበራችሁ የት/ቤታችን የሙያ መምህራን፤ ውብ አዳራሹን የፈቀደልን የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና ከ650 በላይ ጋወኖችን የተባበረን ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክን በትምህርት ቤቱ ስም እናመሰግናለን።
እንዲሁም የየካ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት እና የትምህርቤቱ ወለጅ ኮሚቴ ለመርሃ ግብሩ ማማር ላበረከታችሁልን አሰተዋጽኦ እናመሰግናለን።ለዛሬው 12ኛ ክፍል የምርቃት ፕሮግራም መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የሙያ ትምህርት መምህራን በሙሉ በትምህርት ቤቱ ስም ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ትምህርት ቤቱ::







.