Karalo Secondary School
Announcement እንኳን ደስ አላችሁ!

እንኳን ደስ አላችሁ!

14th September, 2025

(መስከረም 4/2018 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሁሉም ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ችለዋል፡፡

በ2016 የትምህርት ዘመን 21.5 የነበረው በ2017 ዓ.ም 29 ፐርሰንት የሚሆኑት ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግባል፡፡

እንደ ሀገር 100 ፐርሰንት ካሳለፉ 50 ትምህርት ቤቶች መካከል 15ቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡

ምንም ያላሳለፉ ትምህርት ቤት በከተማ አስተዳደሩ የሌሉ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ያስፈተኑ ሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች 100 ፐርሰንት ለማሳለፍ ችለዋል፡፡

ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም 484 የነበሩ ሲሆን በ2017 ዓ.ም 888 ተማሪዎች ሆነዋል፡፡

ሚኒስቴር መስራቤቱ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን በዛሬው እለት አሳውቋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with