Karalo Secondary School
Announcement የ2019 Calender

የ2019 Calender

09th July, 2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2019 ትምህርት ዘመንን በይፋ የሚያበስረውን ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ ለሁሉም ክፍለ ከተሞችና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ያስተላለፈ ሲሆን፣ ተማሪዎችና ወላጆች ካሁኑ ራሳቸውን ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

ይፋ በተደረገው የጊዜ ሰሌዳ የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፣ ለአዲስ ገቢ የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ከነሐሴ 26 እስከ ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም የምዝገባ ጊዜ ተሰጥቷል።

ከዚህም ጎን ለጎን መምህራን በነሐሴ 27/ 2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቶቻቸው ተገኝተው ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የ2019 ዓ.ም የመደበኛ ትምህርት የመጀመሪያ ቀን መደበኛ ትምህርት መስከረም 5/2019 ዓ.ም በይፋ እንደሚጀመር ቢሮው አመልክቷል። (ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክ/ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች እና በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ 3 አዳሪ ት/ቤቶች የላከው ሙሉ የ2019 የትምህርት ካሌንደር ከላይ ተያይዟል)

.

Copyright © All rights reserved.

Created with