Karalo Secondary School
Announcement የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

17th March, 2026

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
(መጋቢት 8/2018 ዓ.ም) ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምዝገባቸውን ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ያሳሰበው አገልግሎቱ፣ ለምዝገባው ሂደት አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችንም ይፋ አድርጓል።
በመመሪያው መሠረት መደበኛ ተፈታኞች በትምህርት ቤቶቻቸው አማካኝነት ምዝገባቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ተፈትነው ውጤት ለማሻሻል ወይም በግላቸው ድጋሚ ለመፈተን የሚፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ በራስ-አገዝ (Self-service) የኦንላይን ዘዴ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
የግል ተፈታኞች ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን https://register.eaes.et የተሰኘ ድረ-ገጽ በመጠቀም ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም ተፈታኝ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልተመዘገበ በስተቀር ለፈተና መቀመጥ የማይችል መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳስቧል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with