የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይጀመራል።
በትምህርት ካላንደሩ መሠረት ዓርብ መስከረም 2/2018 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ክፍት ሆነው መምህራንና ተማሪዎች ውይይት የሚያደርጉበት ነው።
መስከረም 5/2018 ዓ.ም ደግሞ በይፋ ለሚጀመረው የትምህርት ስራ ቅድመ ዝግጅት የሚያደርጉበት ቀን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳታውቋል::
በ2018 የትምህርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች የጀመሩትን የንቅናቄ ተግባር አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና የትምህርት ቤት ምዝገባም እስከ መጨረሻው ቀን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል፡
ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በየትኛውም ክልልና የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ ታብሌትና ማናቸውንም የትምህርት ስራ ላይ ተጽእኖ ሚያሳድሩና አዋኪ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን ተገልጿል
በመሆኑም የትምህርት ተቋማት ይህንን መሰረት አድርገው አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እና ለመምህራርና ተማሪዎቻቸው አስፈላጊውን መረጃ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል::