Karalo Secondary School
Announcement በካራሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 2018 የተማሪዎች የውስጥ ስፖርታዊ ማጠቃለያ መርሃግብር ተከናወነ።

በካራሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 2018 የተማሪዎች የውስጥ ስፖርታዊ ማጠቃለያ መርሃግብር ተከናወነ።

14th May, 2026

ከታህሳስ ጀምሮ በትምህርት ቤታችን ሲካሄድ የነበረው የተማሪዎች የውስጥ የእግር ጨዋታ ውድድር በዛሬው እለት ግንቦት 5 2018 ዓ.ም. በ12ኛ ክፍል እና 9ኛ ክፍል የዋንጫ ጨዋታ ፍጻሜውን አግኝቷል።
በዕለቱ ጨዋታ 12ኛ ክፍሎች 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአመቱ ሻምፒዎን ሆነዋል።
ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ያስተባበራችሁ የስፖርት ክበብ ተጠሪ እና አባል መምህራን፣ በጃኝነት ጨዋታዎችን የመረራችሁና አጠቃላይ ውድድሩ ሰለማዊ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ዩኒት አስተባባሪዎች እና መምህራን እንዲሁም በገንዘብ እና በሃሳብ ድጋፍ ያደረገልን የት/ቤቱ ወተመህ ኮሚቴን ከልብ እናመሰግናለን።
በዋናነት ግን አጠቃላይ የውድድሩ ድምቀት የሆናችሁ ጨዋ እንቁ ተማሪዎቻችን በውድድሩ በመሳተፍም ሆነ በመደገፍ ላሳያችሁን ወርቅ ስነምግባር በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ስም እጅግ በጣም እናመሰግናለን።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with