ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫቸውን ከመስከረም 7/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ ሆነው ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጻል።የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences