በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በስሩ ላሉ የሳይንስ ልህቀት ማዕከል ትምህርት ቤቶች መምህራንን በአፈፃፀማቸውና በትምህርት ውጤታቸው ከሁሉም አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የመንግስት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በማወዳደር መመደብ እና ማሰራ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በሚሰጡ ትምህርት ዓይነቶች 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ዓይነቶችያጠናቀቁና ከመጀመሪያ ዲግሪያቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆነና የመጀመሪያ ዲግሪ መመረቂያ ነጥብ 3.25 እና በላይ በ2ኛ ዲግሪ 3.5 እና በላይ ውጤት ያላቸውን ጠንካራና ምስጉን መምህራን ከየክፍለ ከተማችሁ በየትምህርት አይነቱ አንዳንድ ብቻ በመመልመል ከዚህ በታች በተያያዘው ቅፅ መሰረት እስከ 08/01/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንድትልኩልን ስንል እናሳውቃለን